image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት በሥራ ቦታዎች ላይ ተደራጅተው ለሚሰሩ ኢንተርፕራይዞች የ2019 በጀት ዓመት የውል ማደሻ ጊዜ ከሐምሌ 1/2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም ድረስ መሆኑን በመግለጽ ውላቸውን ያላደሱ አካላት በአስቸኳይ ቀርበው እንዲያድሱ ጥሪ አቀረበ።

ነሀሴ 22, 2018
#ማስታወቂያ:- በክፍለ ከተማው ለምትገኙ ኢንተርፕራይዞች በሙሉ! ጽ/ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 84/2016 በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት የውል ማደስ ሂደቱ የሚመለከተው የአምስት ዓመት የጊዜ ገደብ ያልሞላቸውን ኢንተርፕራይዞች እንደሆነ ያሳወቀ ሲሆን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ውላቸውን በማያድሱት ላይ መመሪያውን ተከተሎ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድም አሳስቧል። -ውል ለማደስ የሚያስፈልጉ ሰነዶች፦ -የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የነዋሪነት መታወቂያ -ነባር የኪራይ ውል እና የታደሰ የደረጃ ዕድገት ማስረጃ -የኪራይ ክፍያ ደረሰኝ -የግቢ ኮሚቴ ግዴታዎችን በአግባቡ መወጣታቸውን የሚያረጋግጥ የኮሚቴ ማረጋገጫ ኢንተርፕራይዞች እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ በማደስ ኃላፊነታችንን እንወጣ!!!

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች