image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ የመስሪያ ቦታዎች አስተዳደር ጽ/ቤት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የሚያስችል የደንብ ልብስ አስተዋወቀ።

ሰኔ 16, 2017
ጽ/ቤቱ የደንብ ልብሱን ያስተዋወቀው የክ/ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ነፃነት ደረሰ በተገኙበት ነው። ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ባስተላለፍት መልዕክት ሪፎርሙን በተገቢው መንገድ በመተግበር አገልግሎት አሰጣጡን የማዘመን ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። የደንብ ልብሱ ለተገልጋዮች ግልፀኝነትን በመፍጠር ረገድ ወሳኝ መሆኑንም ወ/ሮ ነፃነት ገልፀዋል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ሸጉ ተሰማ እንደተናገሩት የደንብ ልብስ መዘጋጀቱ አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ነው ብለዋል። የደንብ ልብሱ ለአገልግሎት አሰጣጡ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ረገድ የማይተካ ሚና አለው ብለው ተቋሙ አገልግሎት አሰጣጡን በየጊዜው ማዘመኑን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አሳስበዋል። ባለሙያዎች በበኩላቸው የደንብ ልብሱ የተሻለ እና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርልናል ሲሉ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች