image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማት እና አስተዳደር ጽ/ቤት ለ17 ኢንተርፕራይዞችና ለ37 አንቀጣቃሾች የመስሪያ ቦታዎችን እጣ በማስወጣት አስተላለፈ

መስከረም 4, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍታለው ከፍያለው በመርሀ-ግበሩ ላይ እንደገለጹት የመስሪያ ቦታዎችን ስናስተላልፍ ለወጣቶች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያሉንን ሀብቶች ፍትሃዊ በሆነ አግባብ ለናንተ ስናስተላልፍና እንድትጠቀሙበት ስንሰጥ ጥሪት አፍርታችሁ እራሳችሁን በኢኮኖሚ እንድታሳድጉ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ መስራት መቻል አለባችሁ በማለት ገልፀዋል። ጽ/ቤቱ ያለውን መስሪያ ቦታ ፍትሀዊነቱን በጠበቀ መልኩ ለዜጎች በማስተላለፍ ችሏል ያሉት አቶ ፍታለው ከፍያለው በተሰጣችሁ መስሪያ ቦታና በመረጣችሁበት የስራ ዘርፍ በመስራት እራሳችሁን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል በማለት ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ የመስሪያ ቦታዎች ልማት እና አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ባህሩ እንደተናገሩት መስሪያ ቦታዎችን ስናስተላልፍ የተላለፈላችሁ ተጠቃሚዎች በተሰጣችሁ ጊዜ ወጤታማ መሆን ይገባል በማለት ለተጠቃሚዎች በንግድ ዘርፍ ለ3 ኢንተርፕራይዞችና ለ9 አንቀሳቃሾች ፣ በማኒፋክቸሪግ ዘርፍ ለ14 ፕራይዞችና ለ28 አንቀሳቃሾች መስሪያ ቦታዎችን ያስተላለፍን ሲሆን ሁሉም መስሪያ ቦታ የተላለፈለት በተሰጠው 5 አመት በመረጠው ዘርፍ ውጤታማ መሆን እንደሚገባ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች