image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለ36 ኢንተርፕራይዝ እና ለ75 አንቀሳቃሾች እጣ በማስወጣት የመስሪያ ቦታዎችን አስተላልፏል።

ህዳር 23, 2017
በልደታ ክ/ከተማ መስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ፅ/ቤት የመስሪያ ቦታዎችን የማስተላለፍ መርሃ ግብር አካሄደ። በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ስራ አስፈፃሚና ስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አራርሳ ድሪባ እንደተናገሩት ሁሉም ተጠቃሚዎች የተላለፈላቸውን የመስሪያ ቦታዎች በአግባቡ በመጠቀም ራሳቸውን ችለው ለሌሎቹም መትረፍ እንደሚገባቸው ገልፀዋል። የመስሪያ ቦታዎች የተላለፈላቸው የተሰጣቸውን መስሪያ ቦታ ለታለመለት ዘርፍ ብቻ ማዋል እኔዳለባቸው የገለፁት አቶ አራርሳ አያይዘው የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም በኢኮኖሚ እራሳቸውን በማሳደግ መሸጋገር እንዳለባቸው ገልፀዋል። በንግድ ለ7 ኢንተርፕራይዞች፣ በማኑፋክቸሪንግ 25 ኢንተርፕራይዞች፣ በከተማ ግብርና 1ኢንተርፕራይዝና በአገልግሎት 3 ኢንተርፕራይዝ በዛሬው እለት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች