image
image
image
image
image

"የኢንተርፕራይዞች ውጤታማነት ለአዲስ አበባ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል የልደታ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ከነባር ኢንተርፕራይዞች ጋር ውይይት አካሄደ።

ታህሳስ 24, 2017
መድረኩን የመሩት የልደታ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አራርሳ ድሪባ እንደተናገሩት በየደረጃው ያሉ ተቋማት በቅንጅት በመሆን የኢንተርፕራይዞችን የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችል ስራን በጥምረት በመስራት ለኢንተርፕራይዞች ፈጣን ምላሽ በመስጠት ውጤታማ ተግባራትን መፈፀም ያስፈልጋል ብለዋል። ኢንተርፕራይዞች መስሪያ ቦታዎችን በአግባቡ በመጠቀም ጥራት ያለው ምርት በማምረት ተወዳዳሪ መሆን ይገባችኋል ያሉት አቶ አራርሳ አያይዘው ለስራቸው እንቅፍት ሊሆኑ የሚችሉ ችግሮችን በጋራ ተቀናጅተን በመስራትና ለጥያቄዎች ፈጣን መልስ መሰጠት ይገባል ብለዋል። ለኢንተርፕራይዞች ስራ እንቅፍት ሊሆኑ የሚችሉ ችግሮችን በጋራ ተቀናጅተን በአጭርና በረጅም ጊዜ በመፍታት ነባር ኢንተርፕራይዞች ምርታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ተቋማትበቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው አቶ አራርሳ ገልፀዋል። ለተነሱ ጥያቄዎችና ሀሳቦች የክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ፣ መስሪያ ቦታዎች አስተዳደር ልማት ጽ/ቤት ፣ ስኬት ባንክ፣..... ከኢንተርፕራይዞች የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት በጋራ በመስራት ይገባል በማለት ገልፀዋል። የውይይቱ ተሳታፊ ኢንተርፕራይዞች በስራቸው ላይ የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት እየተሰራ ያለው ተግባር የተሻለ መሆኑን መግለፅ በቀጣይም በቅንጅት ከዚህ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ አንስተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች