image
image
image
image
image

የ90 ቀን እቅድ አካል የሆነውን የክረምት የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት ተካሄደ።

መስከረም 4, 2017
የልደታ ክፍለ ከተማ መስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት የ90 ቀን እቅድ አካል የሆነውን የክረምት የቤት እድሳት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09 አስጀምሯል ። የቤት እድሳት መርሀ ግብሩ ላይ የልደታ ክ/ከተማ መስሪያ ቦታዎች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ቡርቱካን ባህሩ፣ የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሺበሺ ታምሩ እና እንዲሁም የወረዳው ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በላቸው በተገኙበት አስጀምረዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ መስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ቡርቱካን ባህሩ የ90 ቀን እቅድ አካል የሆነውን በሰው ተኮር ተግባር የአቅመ ደካማ የቤት እድሳት ስራው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል ፡፡ ወ/ሮ ቡርቱካን አያይዘው ይህንን መልካም ተግባር ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበው ይህ የተጀመረው የቤት እድሳት እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች